Teddy Afro

Mematsené
ቀና አታርጉኝ እኔን ከሄደች ትታው መማፀኔን ተክዤ ልግፋው ይሄ ሀዘኔን ጨለማ አልብሳው ስትሄድ የፈካው ቀኔን እኔስ አቅም የለኝም እባክሽ ብዬ ልመልሳት ቢፈጀው ልቤን የፍቅር እሳት አይሞከርም መቼም እሷን ለመርሳት ስትሄድ ስለያት ዛሬ ስሰናበታት ማን አወቀልኝ ውስጤን እንደምወዳት ልሸኛት እንጂ የሆዴን ችዬ ባይል ነው ከላይ ግድ የለም ብዬ ገና በጊዜ በቀዬው አድባር አብረን አድገን ክፋት በሌለው በንፁ ፍቅር ተፈላልገን ተዋደን ኖረን ባልነበር ዓይነት በሚያስቀና ልቧን ከልቤ ድንገት ለያየው ቀን መጣና Letras de canciones በደለኛ ሰው ይቅርታ ብሎ አንሶ ሰው ከካሰ ይኖር ወይ ልቡን ያልመለሰ ሳይገባኝ ለኔ የቱጋ እንደሆን እንኳ ማስቀየሜ ተይ ብያት ነበር ባለኝ አቅሜ መማፀኔ ማሪኝ ማለቴ ለኔም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ ታድያ እንዴት ይሆን ወዳጅን መክሮ ልብን መመለስ ወደ ድሮ መማፀኔ ማሪኝ ማለቴ ለኔም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ ታድያ እንዴት ይሆን ወዳጅን መክሮ ልብን መመለስ ወደ ድሮ ቀና አታርጉኝ እኔን ከሄደች ትታው መማፀኔን ተክዤ ልግፋው ይሄ ሀዘኔን ጨለማ አልብሳው ስትሄድ የፈካው ቀኔን እኔስ አቅም የለኝም እባክሽ ብዬ ልመልሳት ቢፈጀው ልቤን የፍቅር እሳት አይሞከርም መቼም እሷን ለመርሳት ስትሄድ ስለያት ዛሬ ስሰናበታት ማን አወቀልኝ ውስጤን እንደምወዳት ልሸኛት እንጂ የሆዴን ችዬ ባይል ነው ከላይ ግድ የለም ብዬ በዚያ በሚዛን ነፍስ ያለፍቅር መች ይሞላል በሌለሽበት ሲኖር ያላንቺ ቀን ይጎላል እስኪ አውቀንበት ሰው ሳንፈልግ ሌላ ዳኛ ብለን ለፍቅር ተይ እንገናኝ ዞረን እኛ በደለኛ ሰው ይቅርታ ብሎ አንሶ ሰው ከካሰ ይኖር ወይ ልቡን ያልመለሰ ሳይገባኝ ለኔ የቱጋ እንደሆን እንኳ ማስቀየሜ ተይ ብያት ነበር ባለኝ አቅሜ መማፀኔ ማሪኝ ማለቴ ለኔም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ ታድያ እንዴት ይሆን ወዳጅን መክሮ ልብን መመለስ ወደ ድሮ መማፀኔ ማሪኝ ማለቴ ለኔም ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ ታድያ እንዴት ይሆን ወዳጅን መክሮ ልብን መመለስ ወደ ድሮ From Letras Mania